Podder

የእግዚአብሔር መንግሥት

by Kassa Keraga

Inactiveen·28 episodes
religionspiritualitychristianity

Listener stats

Estimated listeners
Pro

About

<p>‹‹እውነት ባዕድ(እንግዳ) ከሆነ ስፍራ ሊገኝ እንደሚችል ጓደኞቼ አስጠንቅቀው ነግረውኝ ነበር፡፡›› ዴቪድ ኒኮላስ</p><p>‹‹እስከ ዛሬ ብዙ የተማራችሁት፣ የሰማችሁትና ያነበባችሁት ያወቃችሁትም ሊኖር እንደሚችል እናውቃለን፡፡ ግን እስቲ እንደ ገና እነዚህን ገጾች ትሰሙን ዘንድ እንለምናችሁ፡፡ በገዛ ዘመኗ ጳውሎስ የሚናገረውን ለማዳመጥ ጌታ ልቧን እንደ ከፈተላት እንደ ሊዲያ ልባችሁን ይከፍተው ዘንድ እንጸልያለን፡፡ ሁሉን አዲስ ከሚያደርገው ጌታ ጋር እስቲ የእውቀቱን ቀንዲል እንደ ገና ለኩሱት፡፡ አዲስ ሰማይ (ልብ) እና አዲስ ምድር (ምልልስ) ይሆንልን ዘንድ በዚህ በዘመነ ሎዶቅያ ሌላ ዕድል ተሰጠን፡፡ ዘመንም ብቻ ሳይሆን የተሰጠን የዘመኑ መልእክተኞችም አሉን፡፡</p><p>አስቀድመን ከሰማነው ሌላ እንዳንሰማ ካመረርንበት ከተማችን መመለስና መውጣት አለብን፡፡ ስለ ወጋችን - ስለ ትምህርታችን - ስለ ‹‹አባቶች›› ቀኖና - ስለ አንድ ዘመን ብርሃን (እውነት) በግትርነት ጸንተን የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻርና ለመዋጋት ያደረግነው የነፍስ ተጋድሎ ማብቃት አለበት፡፡ ለመንፈሳዊ ሃፍረታችን እራፊ ጨርቅ እንኳ ያሳጣንን የዛሬውን ‹‹መንፈሳዊነት›› ልንታገሠው የቻልነው በምን ልብ ነው? መንፈሳዊነት ማፈሪያ፣ እንቅስቃሴም የገዛ ምኞት ባሪያ፣ አገልግሎት ደግሞ ቅሌት… ዋጋቸው ባደረጉበት በዚህ ዘመን… በእነዚህ ገጾች ያሉትን ጽሑፎች ማንበብና መልእክቶችን ማዳመጥ ልዩነት ያመጣሉ ብለን እናምናለን፡፡ በእናንተ ልዩነት ባያመጣ እንኳ ዘመናችሁን ግን እንደሚኮንነው እርግጠኞች ነን፡፡</p><p>የምንላችሁም ብዙ ነገር አለንና ነፍሳችሁ እንጂ መንፈሳችሁ አይጥበብብን - የሚቤዥ ጌታ ያድርገው - አሜን!!</p>

Most recent episode